ወደ ዋናው ይዘት ዝለል
Lehulum SACCOS

ስለ ማህበራችን

እኛ ማን እንደሆንን፣ ምን ላይ እንደምንቆምና አባላትን እንዴት እንደምናገለግል ይወቁ።

እኛ ማን ነን

ለሁሉም ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር አባላቱ በአንድነት የሚቆጥቡበትና የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት፣ በትብብር መንፈስ እርስ በርስ የሚደጋገፉበት የአባላት የገንዘብ ህብረት ሥራ ማህበር ነው።

ቁጠባና ልማት በጋራ

አባላት በጋራ ሲቆጥቡ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአባላት ብድር ለመስጠት ሊያገለግል ይችላል። ይህ የቁጠባና የብድር ዑደት ቤተሰቦችና አነስተኛ ንግዶች እንዲያድጉ ሊረዳ ይችላል፤ የባለቤትነትና የውሳኔ ሥልጣኑም በአባላት እጅ ይቆያል።

የለሁሉም ቁጠባና ብድር ህ/ሥ/ማህበር ምልክት
ከማህበሩ ደንብ

ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማና ዋና ዋና ተግባራት

ራዕያችን

እስከ 2025 ዓ.ም በሥራ ክልሉ የሚገኙ ማህበረሰቦችን በሙሉ በአባልነት በማቀፍ፣ የቁጠባ ባህልን በማዳበር፣ ጠንካራና ተደራሽ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን እንዲሁም አባላትን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ በማሳተፍ የኑሮ ደረጃቸው ተሻሽሎ ማየት።

ተልዕኳችን

በሥራ ክልሉ የሚገኙ ማህበረሰቦችን በሙሉ በአባልነት ማቀፍ፣ የተለያዩ የቁጠባ አገልግሎቶችን መስጠት፣ ለአባላት የሚፈለገውን ብድር በማቅረብ ጠንካራ የፋይናንስ ምንጭ መፍጠር እና አባላት ከዚህ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ።

ዓላማችን

  1. ከአባላትና ከሌሎች የፋይናንስ ምንጮች ገንዘብ በማሰባሰብ፣ አባላት በኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ የብድር ፋይናንስ ምንጭ መሆን።
  2. የቁጠባ ባህልን በማሳደግ ራስ መተማመንንና የአባላትን ተጠቃሚነት ማጠናከር።

ዋና ዋና ተግባራችን

  1. የአባላትን የመመዝገቢያ ክፍያና የተለያዩ ገቢዎችን መሰብሰብ፤
  2. ከአባላት የአገልግሎትና ሌሎች ክፍያዎችን መሰብሰብ፤
  3. ለአባላት ድርሻ (shares) መሸጥ፤
  4. መደበኛ፣ የሕፃናት፣ የሴቶችና የፍላጎት ቁጠባዎችን ከአባላት መሰብሰብ፤
  5. የተለያዩ የቁጠባ ዓይነቶችን (የሕፃናት ቁጠባ፣ የጊዜ ገደብ ቁጠባና ሌሎች) መሰብሰብ፤
  6. ለአባላት ብድር መስጠት፤
  7. የተሰጠ ብድርን መሰብሰብ፤
  8. ለአባላት የቁጠባ ወለድ መክፈል፤
  9. የገንዘብ ማስተላለፍ (Money Transfer) አገልግሎት መስጠት፤
ከማህበሩ ደንብ

እሴቶችና የሥነ-ምግባር እሴቶች

እሴቶቻችን

ማህበሩ በሥራው ሂደት ውስጥ የሚከተሉትን እሴቶች በተግባር ላይ ያውላል፦

  • ራስን መርዳት (በራስ መተማመን)
  • ራስን ተጠያቂ ማድረግ
  • ዴሞክራሲያዊ አሰራርን ማስፋፋት
  • እኩልነት
  • ፍትሃዊነት
  • አንድነት

የሥነ-ምግባር እሴቶቻችን

አባላት፣ የሥራ አመራር ኮሚቴዎችና ሌሎች የሥራ ክፍሎች የሚከተሉትን የሥነ-ምግባር እሴቶች ማክበርና መከተል ይኖርባቸዋል፦

  • ታማኝነት
  • ግልጽነት
  • ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት
  • ሌሎችን ማሳተፍ
  • ለማህበረሰቡ መጨነቅ
  • ለሌሎች ማሰብ (አሳቢነት)

ለአባላት ያለን ቁርጠኝነት

ለእያንዳንዱ አባል ክብር በመስጠት፣ አገልግሎቶቻችንን በግልጽ በማስረዳትና ጥያቄዎችንና አሳሳቢ ጉዳዮችን በትኩረት በማዳመጥ ለመሥራት እንተጋለን።

  • አገልግሎቶቻችንን በግልጽና በታማኝነት ለማስረዳት እንተጋለን።
  • ለእያንዳንዱ አባል ክብር ለመስጠት እንተጋለን።
  • ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችንና ቅሬታዎችን በትኩረት እናዳምጣለን።

ስማችን

አማርኛ
ለሁሉም ቁጠባና ብድር ህ/ሥ/ማህበር
ለሁሉም የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የሕ/ስራ ማህበር
ኦሮምኛ
QUSANNOO FI LIQII LAHUULLUM I/G/K/MURTAA'EE
እንግሊዝኛ
Lehulum Savings and Credit Limited Liability Cooperative Society

ለመቆጠብ ዝግጁ ነዎት?

አባል እንዴት መሆን እንደሚቻልና የትኛው አማራጭ እንደሚስማማዎት ለማወቅ ያግኙን።